ስፓርት

የካፍ ፕሬዚዳንት አሕመድ አህመድ የአምስት አመት እግድ ተላለፈባቸው

By Tibebu Kebede

November 23, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት አሕመድ አህመድ ላይ የአምስት አመት እገዳ አስተላለፈ፡፡

ፊፋ ፕሬዚዳንቱ ከገንዘብ እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ናቸው ብሏል፡፡

የፊፋ የስነ ምግባር ኮሚቴም አህመድ አህመድ ከታማኝነት እና ከጥቅም ጋር የተያያዙ ደንቦችን ጥሰዋል ነው ያለው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፕሬዚዳንቱ ላይ የአምስት አመት እግድ አስተላልፏል፡፡

የ60 ዓመቱ አህመድ አህመድ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡