የሀገር ውስጥ ዜና

መከላከያ ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጠረ

By Tibebu Kebede

November 22, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጥሯል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቀሌን ለመያዝ እየገሠገሠ ነው።

የመከላከያ ሠራዊቱ ከሰሞኑ ሽሬን፣ አክሱምን፣ አድዋንና አዲግራትን ከጁንታው ነጻ ማውጣቱ ይታወቃል።