አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስግብግብ ጁንታው የመቀበሪያ ጉድጓዱ አፍ ላይ ቆሞም ውሸት መናገሩን ቀጥሏል አሉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ።
የጁንታው ‘ቀንደኛ’ መሪዎች ግን እየተንቀጠቀጡ የሚሰጡት የውሸት መግለጫ ውሸት ለሚግቱት ደጋፊያቸው ናፍቆታል ሲሉ በማህበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል።
ውሸታቸውን በውሸት ለዋውሰው የሚግተቱ ዲጂታል ወያኔም ግራ ተጋብቷል ብለዋል።
የሚመኩባቸው ተራሮችም የውሸታም መደበቂያ ሳይሆን መቀበሪያ ነን በሚል ክደዋቸዋል ነው ያሉት።
ሀገር የዘረፈ ሌባ፣ የንፁሀንን ደም ያፈሰሰ ጨካኝ፣ ከእኔ በላይ ላሳር የሚል እብሪተኛ፣ መግደል እንጅ መሞትን እስካሁን ያልቀመሰ አረመኔ፣ ትዕግስትን እንደ ፍርሀት የሚቆጥር ጅላጅል፣ በሌሊት ጓዱን የሚረሽን ነውረኛ እኛ ጋር አይጠለልም ብለዋል ተራሮቹ ሲሉም ይገልፃሉ ዋና ዳይሬክተሩ።
ለፍትህና ለእውነት የቆሙትን ግን ከለላና መከታ እንደሆኑላቸው ይናገራሉ።
አቶ ተመስገን እውነት የጁንታው ቀንደኛ መሪዎች በሌሊት ያስረሸኑት ሰራዊት አፈሙዝ ፊት ሊገኙ ወይስ ራሳቸውን ቱቦ ውስጥ ሊደብቁ? እናያለንም ነው ያሉት::