Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሚድሮክ ግሩፕ የተገነባው ባለ 25 ፎቅ ህንጻ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሚድሮክ ግሩፕ የተገነባው ባለ 25 ፎቅ ህንጻ ስራ ጀምረ
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ÷በሚድሮክ ግሩፕ በከተማችን ውብ ሆኖ ተገንብቶ ለ13 አመታት ያለ ስራ ቆሞ የነበረውን ባለ 25 ፎቅ ሚና ህንጻን ዛሬ ስራ በማስጀመራችን ደስ ብሎኛል ብለዋል።
በሚና ህንጻ አዲስ የተከፈተውን የተለያዩ የሃገራችንን ምርቶች በአንድ ቦታ ለሸማቾች እንዲቀርብ እየሰራ ያለውን ኩዊንስ ሱፐር ማርኬትንም መርቀናል ነው ያሉት።
ከንቲባዋ አያይዘውም የእንደዚህ አይነት የዘመናዊ የችርቻሮ አውታር መብዛትና መስፋፋት የነዋሪያችን የገበያ ፍላጎት በማሟላት በአምራችና ሸማች መሃከል ያለውን የግብይት ሰንሰለት ያሳጥራል ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ እንዲሁም የስራ እድልን በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና አለውም ነው ያሉት።
በጦር ሃይሎች አካባቢ የተከፈተውን ተመሳሳይ የገበያ ማዕከል ከወር በፊት ጎብኝተናል በሌሎች አካባቢም እንዲከፈቱ ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት ተግባራዊ ምላሽ ስለሰጡ የሚድሮክ ግሩፕ አመራሮችን ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።
አሁንም እንዲህ አይነት የህዝቡን ኑሮ መደጎም የሚችሉ ኢንቨስትመንቶችን እናበረታታለንም ነው ያሉት።
Exit mobile version