አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ማስረዳታቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፅህፈት ቤታቸው በኩል እንዳስታወቁት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ስለደረሰው ጥቃት እንዲሁም በዜጎች የጅምላ ጭፍጨፋ ዙሪያ ለደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሚገባ አስረድተዋል፡፡
ወዳጆች እና አጋሮች እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ላሳዩት መቆርቆር እናመሰግናለን ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ራማፎሳ በወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ ለመወያየትም ልዩ ልኡክ ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውንም አስታውቀዋል።
የአፍሪካ ህብረት በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ድርድርን በማመቻቸት እየሰራ ላለው ስራ ፕሬዚዳንቷ አመስግነዋል።