አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ መቀመጫቸውን በታንዛኒያ ካደረጉ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ።
አምባሳደር ዮናስ በታንዛኒያ ከኳታር፣ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች፣ አልጀሪያ እና ከአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ ስላለው ህግን የማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ለአምባሳደሮቹ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
በዚህ ወቅትም ለእርምጃው መንስኤ ስለሆኑ ምክንያቶች፣ አጠቃላይ ሁኔታው እና የእርምጃውን ግብ በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።