በደምቢዶሎ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህግ ማስከበር ተልዕኮን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

By Tibebu Kebede

November 20, 2020

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህግ ማስከበር ተልዕኮን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ፡፡

በዛሬው ዕለት በተካሄደው ሰልፍ ላይ የህወሓት የጥፋት ቡድን በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመውን ክህደት አውግዘዋል፡፡

የቡድኑ ባህሪ የአጥፍቶ ጠፊ በመሆኑ ሀገራዊ ክህደት በመፈፀም መከላከያን ከጀርባው ወግቷል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ሀገር ለማፍረስ የሚፈፅመውን ጥፋት ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እናከሽፋለን ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ሰልፈኞቹ መንግስት የሀገር ሉዓላዊነትንና የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚያካሂደውን ዘመቻ እንደግፋለንም ነው ያሉት፡፡