Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢጋድ ቀጠናዊ ትስስር ለማምጣት ባለው ሚና ላይ ያተኮረ የዌቢናር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ቀጠናዊ ትስስርን ለማምጣት ባለው ሚና ላይ ያተኮረ የዌቢናር ውይይት ተካሄደ፡፡
ውይይቱን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢጋድ ሴክሬታሪያት ጋር በመተባባር ያዘጋጀው ነው ተብሏል፡፡
በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን አምባሳደር መሐመድ ሃሰን መሰል መድረኮች በቀጠናው ኢጋድ እየወሰዳቸው ስላሉ ዘርፈ-ብዙ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ዲፕሎማቶች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡
የኢጋድ የኢኮኖሚ ትብብር እና ቀጠናዊ ትስስር ዳይሬክተር ኤልሳዲግ አብደላ በበኩላቸው፥ የኢጋድ ተቀዳሚ ግብ በቀጠናው ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በቀጠናዊ ትስስርና ፖሊሲ አስተዳደር እንዲሁም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማሳደግ በሚቻልባቸው አግባቦች ዙሪያ ምክክር መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version