Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቦርዱ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር አደርጋለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ በትግራይ ክልልና አጎራባች አካባቢዎች ኢ-ስበአዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታወቀ።
በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ መርማሪ ቦርድ መቋቋሙ ይታወሳል።
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተለይም ከህዝብ ደህንነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያሻው ነው” ብለዋል።
ቦርዱ በአጠቃላይ ያከናወናቸውን ስራዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑንና በተለይም በትግራይ ክልልና አጎራባች አከባቢዎች ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
በአዋጁ የተቀመጠው የቦርዱ የስራ ወሰን ትግራይ ክልል ቢሆንም የመርማሪ ቦርዱ ግብረሀይል ከክልሉ ውጪም ተያያዥ የሆኑ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን የመከታተልና ሃላፊነት እንደተሰጠው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም መቋቋሙ ይታወሳል።
Exit mobile version