የሀገር ውስጥ ዜና

ጀርመን ለጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 1 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

By Tibebu Kebede

November 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመን ኤምባሲ ለጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 1 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ፡፡

የሆስፒታሉ የመድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መካንቴ የተደረገው ድጋፍ ለሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ከፍ ያለ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ይህም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል ፡፡

የጀርመን  መከላከያ ሰራዊት ቴክኒካል አማካሪ ቡድን ሀላፊ ኮሎኔል አንደሬ ስኮፊስ በበኩላቸው ድጋፉ ወደ ፊትም እንደሚቀጥልና የሀገራቱን ወታደራዊ ግንኙነት ማሳያ እንደሆነ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።