አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን “ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን” በሚል ለሰራዊቱ ያላትን ድጋፍ ገለጸች።
“ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን” በሚል መሪ ቃል የተላለፈውን ጥሪ በመቀበል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን ድጋፍና ክብር ገልጿል።
መርሐ ግብሩ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።
በመርሐግብሩ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከመከላከያ ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውንና ለሀገር ሰላምና አንድነትም የበኩላቸውን እንደሚያበረክቱ ቃል መግባታቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።