Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ እና የኢፌዴሪ ጦር
ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
መርሃ ግብሩ ከረፋዱ 5:30 ላይ በተለያዩ ስፍራዎች ለሁለት ደቂቃ የተካሄደ ሲሆን ከዚያ ቀደም ብሎ የተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተካሄደዋል፡፡
በአላዘር ታደለ
Exit mobile version