Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተጨማሪ 509 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 303 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ5 ሺህ 532 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 509 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 101 ሺህ 757 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በዚህም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 558 ደርሷል።

በሌላ በኩል እስካሁን 63 ሺህ 571 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ባለፈ 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ የአራት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 558 ደርሷል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 36 ሺህ 626 ሰዎች መካከል 316 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ ናቸው።

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 550 ሺህ 663 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

Exit mobile version