በህዳር 4/2013 ዓ.ም ከቤይሩት የተመለሱ ኢትዮጵያውያን

የሀገር ውስጥ ዜና

84 ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ከቤሩት ተመለሱ

By Abrham Fekede

November 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 84 ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ከቤይሩት – ሊባኖስ ወደ ሃገራቸው በሰላም መግባታቸው ተገለጸ፡፡

ሊባኖስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽህፈት ቤት ይፋ እንደደረገው አሁን የተመለሱት ዜጎች ከዚህ ቀደም የተመዘገቡ ናቸው፡፡

በዘጠነኛ ዙር ለመመለስ ከተመዘገቡት መካከል 84 የሚሆኑት ሰነድ አልባ መሆናቸውንም ቆንስሉ ጨምሮ አስታውቋል፡፡