ስፓርት

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ በኒጀር አቻቸው 1 ለ 0 ተሸነፉ

By Tibebu Kebede

November 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ በኒጀር አቻቸው 1 ለ 0 ተሸነፉ::

የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ከኒጀር ጋር በኒያሚው ስታድ ጀነራል ሴኒ ስታዲየም አድርገዋል፡፡

በጨዋታው ኒጀሮች ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ አይቮሪ ኮስት ከማዳጋስካር ያደረጉት ጨዋታ በአይቮሪኮስት 2 ለ 1 አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።