ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአውስትራሊያ  ሰደድ እሳት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው

By Tibebu Kebede

December 29, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውስትራሊያ በተነሳው እሳት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የቪክቶሪያ ከተባለ  ግዛት ለቀው እንዲወጡ  መነገሩ ተሰማ።

በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ ግዛት ውስጥ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በጫካ የተነሳው ሰደድ እሳት እየተባባሰ በመምጣቱ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል፡፡

ሰኞ የአየር ሁኔታው 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ መሆኑ ብቻ ሳይሆን  ኃይለኛ ነፋስ ፣ ነጎድጓዶች እና የነፋስ  አቅጣጫ ለውጥ ሊያጋጥም  እንደሚችልም ነው የተነገረው።

የአደጋ ጊዜ ሀላፊው አንድሪው ክሪስፕ እንዳሉት በምስራቅ ጊፕላንድላንድ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሰኞ ጠዋት በማለዳ  አካባቢውን ለቀው መውጣት አለባቸው ብለዋል።

በመላው አውስትራሊያ ከ100 የሚበልጡ የሰደድ እሳቶች በተለያየ ቦታ መቀስቀሳቸውን ቀጥለዋል ነው የተባለው።

ትልቁ እሳት በሲድኒ ከተማ አቅራቢያ  በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ የተነሳው ነው።

ከሩብ ሚየዮን የሚበልጡ ሰዎች ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሚደረጉ ርችቶች እንዲሰረዙና ገንዘቡ የተነሳውን እሳት ለመከላከል እንዲውል ፊርማ በማሰባስብ ጥሪ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ታውቃል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ