Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ 8 ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮች በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ስምንት ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮች በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሊገነቡ  መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኒጅኒነር ታከለ ኡማ በመጪው ሳምንት ጎተራ አካባቢ ግንባታው የሚጀመረውን እና “አፋር መንደር” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ፕሮጀክት ላይ ያለውን ዝግጅት ተመልክተዋል።

የአፋር ተወላጅ በሆኑ ባለሀብቶች በጎተራ አካባቢ የሚገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የግል ይዞታቸው በሆነ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው ተብሏል።

መኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን እና አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን እንደሚያካትት ታውቋል።

ከዚህ ቀደም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በቻይና ኩባንያዎች የሚገነቡ ሁለት ግዙፍ የመኖሪያ መንደሮች ይፉ መደረጋቸው ይታወሳል።

ከዚህ ጎን ለጎንም የመኖሪያ መንደር ግንባታዎቹ ላይ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች እየተሳፉ ይገኛሉ።

ይህን አፋር መንደር የተባለ ስያሜ የተሰጠውን መንደር ጨምሮ 8 የመኖሪያ መንደሮች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በቅርብ ጊዜያት እንደሚጀመሩም የከንቲባ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።።

እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን ከማበረታታት ባሻገር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ያለሙ መሆናቸውም ታውቋል።

 

Exit mobile version