Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ከ290 በላይ ሰንጋና ፍየል ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለአማራ ልዩ ሀይል ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ከ290 በላይ ሰንጋና ፍየል ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለአማራ ልዩ ሀይል ድጋፍ አደረጉ፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ አንማው ዳኛቸው÷ ከዞኑ ስምንት ወረዳ ነዋሪዎች ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም በ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር 134 ሰንጋ፣ 156 ፍየልና 10 በጎችን በመግዛት እንዲሁም 3 መኪና ደረቅ ምግብ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን ማዕከላዊ ጎንደር የሚገኘው የሎጀስቲክ ስምሪት ይረከባልም ነው ያሉት አቶ አንማው፡፡

ዞኑ ከዚህ በፊትም መሰል ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሰዋል፡፡

 

በናትናኤል ጥጋቡ

Exit mobile version