የሀገር ውስጥ ዜና

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ግለሰቦች ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳሰበ

By Tibebu Kebede

November 12, 2020

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ግለሰቦች ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

ጽህፈት ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ “እውቅና ያላቸውን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጨምሮ ሁሉም ግለሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያንፀባርቅና ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠብ እናሳስባለን” ብሏል።