አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አብርሀም አለኸኝ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ።
የክልሉ ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው።
ይህንን ተከትሎም አቶ አብርሃም አለኸኝ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሆነው በዛሬው ዕለት መሾማቸውን ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አቶ አብርሃም የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።