ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት በትንሹ 76 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

By Tibebu Kebede

December 28, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት በትንሹ 76 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

ጥቃቱ የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚበዛበት የፍተሻ ጣቢያ አካባቢ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተፈጸመ ነው።

ፖሊስ በበኩሉ ጥቃቱ በከተማዋ የሚገኝን የግብር መሰብሰቢያ ማዕከል ኢላማ ያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪም ከ100 በላይ ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል ነው የተባለው።

ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በታጣቂው አልሸባብ ሳይፈጸም አልቀረም ተብሏል።

በዚህ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር አሁን ካለው በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ነው የተነገረው፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ እና ቢቢሲ