የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሾሙ

By Tibebu Kebede

November 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሾሙ።

ርእሰ መሥተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሌላ ኃላፊነት መታጨታቸውን ተከትሎ ለክልሉ ምክር ቤት የስልጣን መልቀቂያ በማስገባታቸው  ጥያቄያቸው በምክር ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን  አብመድ ዘግቧል።

ይህንን ተከትሎም በምትካቸው የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በእጩነት ያቀረባቸው በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አገኘው ተሻገር የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል፡፡