አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴሞክራቱ ዕጩ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
ጆ ባይደን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን በማሸነፍ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጠዋል ነው የተባለው።
ባይደን በፔንሲልቬኒያ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆናቸውም ተረጋግጧል።
በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ባይደን 273 ኤሌክቶራል ድምጽ ማግኘታቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።