አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል 389 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት 200 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት በመስኖ ልማቱ ስንዴን በስፋት ለማልማት 4 ዞኖች ተለይተዋል።
በዞኖቹ 18 ወረዳዎች ላይ ስንዴን በስፋት ለማምረት እና የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና እና መሰረታዊ ፍጆታ ለማሟላት ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።
ይህም ሀገሪቱ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በራስ አቅም ለመሸፈን እና ለማምረት ለያዘችው እቅድ አቅም እንደሚፈጥር ተስፋ ተጥሎበታል ነው ያሉት።
በተጨማሪም በክልሉ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ከክልሉ እና ከፌደራል መንግስት እንደተመደበ ተናግረዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን