የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ተደራራቢ የከተማ ግብርና ማሳያ ስፍራን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

December 27, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተደራራቢ የከተማ ግብርና ማሳያ ስፍራን ጎበኙ።

ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ጋር ባደረጉት ጉብኝት በጥቂት ስፍራዎች በርካታ ምርቶች ማምረት የሚያስችለውን ተደራራቢ የግብርና ስፍራን ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሞች ለከተማ ግብርና ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም በተለይም ለፍጆታነት የሚውሉ አትክልቶችን ለማብቀል መጠቀም ይገባል ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።