አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአሜሪካ በትናንትናው ዕለት ብቻ 102 ሺህ 591 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ወረርሽኙ ከተከሰተበት ወቅት ጀምሮ በአንድ ቀን ይህን ያህል ሰው ሲያዝ የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡
በተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ ሆስፒታሎች በህመምተኞች እየተጨናነቁ መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል፡፡
በኮሎራዶ በኢንዲያና፣ በሚቺጋን፣ በዋሽንግተን እና በሌሎች አምስት ግዛቶች በአንድ ቀን ብዙ ሰው እንደተያዘባቸው ነው የተገለጸው፡፡
በመላው አሜሪካ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያሳያሉ፡፡
አሁን ላይ በሃገሪቱ በየዕለቱ በአማካይ 850 ሰዎች በወረርሽኙ አማካኝነት ህይወታቸውን ያጣሉ ነው የተባለው፡፡
በጥቅሉ በአሜሪካ እስካሁን 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 233 ሺህ 663 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን እንዳጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ