አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በበይነ መረብ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሶስትዮሽ ውይይት በዛሬው ዕለት አካሂደዋል።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በበይነ መረብ በሀገራ መካከል የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ታዛቢዎች እና የአፍሪካ ህብረት የመደባቸው ባለሙያዎች ተሳታ ሆነዋል።
በዚህ ውይይት በድርድሩ አካሄድ ዙሪያ በሀገራቱ ባለሙያዎች መካከል ላለፉት ሁለት ቀናት የተደረገው ምክክር ሪፖርት ለውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች መቅርቡ
ተጠቁሟል።
ሚኒስትሮቹም በቀጣዩ ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና እና የስራ ቢጋር፣ የድርድር መነሻ ስለሚሆን ሰነድ እና የጊዜ ሰሌዳ ትኩረት በማድረግ ተወያይተዋል።
ውይይት በተደረገባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ በድርድሩ ቀጣይ አካሄድ ዙሪያ ለመምከር ለአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት ሊቀመንበር እና ለደቡብ አፍሪካ ሶስቱ ሀገራት የተናጠል ሪፖርት እንዲያቀርቡ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው።