አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትህነግ በአማራ ክልል ሶሮቃና ቅራቅር አካባቢ ያደረገው የጦርነት ሙከራ በአማራ ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መክሸፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በመንግስት እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አስመልከቶ በሰጡት መግለጫ ምሽቱን በሰሜን ዕዝ መከላከያ ካምፖችና የተለያዩ መሰረተ ልማት ያሉባቸው አካባቢዎች የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የተቀናጀ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልፀዋል።
በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅራቅር አካባቢ ትህነግ የጦርነት ሙከራ ማድረጉንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ልዩ ኃይልም ሙከራውን ሙሉ በሙሉ አክሽፎታልም ነው ያሉት፡፡
ትህነግን ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ለሚወሰደው እርምጃም ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመሆን እንዲያግዝና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡