Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዋሽ ወልዲያ የባቡር ፕሮጀክት ላይ የሚገኙ ዋሻዎች ሥራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዋሽ ወልዲያ የባቡር ፕሮጀክት ላይ የሚገኙ የ12ቱም ዋሻዎች ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ።
 
የ12ቱም ዋሻዎች አጠቃላይ ርዝመት ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ነው ተብሏል፡፡
 
ረዥሙ ዋሻ በወልዲያ አካባቢ የሚገኘው ሲሆን 2 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይሸፍናል፡፡
የፕሮጀክቱ ወቅታዊ የአፈጻጸም ደረጃም 91 ነጥብ 88 በመቶ መድረሱን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Exit mobile version