አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የመኖሪያና ሥራ ፈቃድ ህግን ተላልፈው የተገኙ ስምንት ታዳጊ ወጣት ዜጎችን ከእስር ማስፈታቱን አስታወቀ።
ኤምባሲው ሪያድ ከተማ በህግ አስከባሪ ተይዘው የነበሩ ዜጎችን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገርና ሃላፊነት በመውሰድ እንዲፈቱ ማድረጉን አስታውቋል።
በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት የታመሙ ዜጎች ከተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲፈቱ በማድረግና በሃላፊነት በመቀበል ዘመዶቻቸው ጋር እንዲሆኑና የህክምና ክትትል እንዲያገኙ ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሷል።
በተመሳሳይ በህመም ላይ የነበሩ ሁለት ዜጎች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ከነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ እንዲፈቱ አድርጓል።