Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በካዛኪስታን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ14 ሰዎች ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በካዛኪስታን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ በጥቂቱ 14 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

ንብረትነቱ ቤክ ኤር የተሰኘው አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ መከስከሱ ነው የተነገረው።

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ 60 ሰዎች መጎዳታቸውም ተገልጿል።

አውሮፕላኑ ከአልማቲ ከተማ ወደ መዲናዋ ኑር ሱልጣን ለማምራት እንደተነሳ ባለሁለት ወለል ህንጻ ጋር ተጋጭቶ አደጋው መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል።

የአደጋው መንስኤም እስካሁን አልታወቀም ተብሏል።

አደጋው በተከሰተበት ወቅት በአካባቢው ጭጋጋማ አየር እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Exit mobile version