ፋና ስብስብ

4ኛው የኦዳ አዋርድ የሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄደ

By Tibebu Kebede

October 29, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አራተኛው የኦዳ አዋርድ የሽልማት ስነ ስርአት ትናንት ምሽት ተካሂዷል።

የሽልማት ስነ ስርዓቱን በሻቱ ቶለማርያም መልቲ ሚዲያ ከኦሮሚያ ክልል  ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑም ተገልጿል።

በርካታ የኪነ ጥበብ ሰዎች እና አፍቃሪያን በተገኙበት የተካሄደው የዘንድሮው የኦዳ አዋርድ የሽልማት ስነ ስርዓት መታሰቢያነቱ ለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ተደርጓል።

የሽልማቱ አዘጋጅ ጋዜጠኛ በሻቱ ቶለማርያም፥ የዘንድሮው ሽልማት በኮቪድ 19 ምክንያት በነበረው አጭር  ሙዚቃ ላይ ብቻ ማተኮሩን ገልፀዋል።

በቀጣይ ግን ሌሎች የጥበብ ዘርፎችም ይካተታሉ ብለዋል።

በዚህኛው ሽልማት ከተካተቱት ዘርፎች መካከል የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ ፣ የዓመቱ ምርጥ ቪድዮ ክሊፕ፣ የዓመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ፣ የዓመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊ፣ የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ጥምረት፣ የዓመቱ ምርጥ ተፅእኖ ፈጣሪ አርቲስት እና የህይወት ዘመን ተሸላሚ ይገኙበታል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ