አዲስ አበባ፣ታህሳስ 16፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኢትዮጵያ 20ዓመት በታች የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መስጠቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
ከታህሳስ 14 እስከ 16 የቆየው ስልጠና የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ እና ልማት ዳይሬክቶሬት መስጠቱ ታውቋል፡፡
በሀገር ውስጥ ኢንስትራክተሮች የተሰጠው ስልጠና በንደፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ነበር ተብሏል፡፡
በ2012 ከሚካሄደው የኢትዮጵያ ወጣቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር በፊት ለአሰልጣኞች ማነቃቂያ ለመስጠትና በቀጣይ ለሚታሰበው ከ20 ኣመት በታች የአፍሪካ ውድድር በየክለቡ የሚገኙ ወጣቶችን ብቁና ዝግጁ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በዚህ ስልጠና ላይ 17 ክለቦች መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡