የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 602 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 918 ሰዎች አገግመዋል

By Tibebu Kebede

October 28, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ6 ሺህ 290 ሰዎች የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ተደርጎ 602 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሌላ በኩል 918 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 49 ሺህ 886 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

በተጨማሪም የስድስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 451 ደርሷል።

አሁን ላይ 43 ሺህ 481 ሰዎች ቫይረሱ የሚገኘባቸው ሲሆን 315 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 94 ሺህ 820 ደርሷል።