አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ ለሚገነባው የኤርትራ ኤምባሲ ህንፃ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
ሀምሌ 19 መናፈሻ አካባቢ ለሚገነባው ለዚህ ኤምባሲ ሁለቱ መሪዎች የመሰረት ድንጋዩን በጋራ አስቀምጠዋል። በዚህም ወቅት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት የኤምባሲ መገንቢያ ቦታው ለኤርትራ ህዝብና መንግስት የተሰጠ ስጦታ መሆኑን አብስረዋል።