አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡
ለረጅም አመታት በስዕል እና በተለያዩ የአርት ስራዎች ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩት ክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስ ለማ ጉያ፥ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል፡፡
አርቲስት ለማ ጉያ የኢትዮጵያን እንዲሁም የኦሮሞን ህዝብ ባህልና ማንነት በዓለም አደባባይ እንዲታወቅ እንዲሁም አፍሪካዊነትን ከፍ አድርገው የሚያሳዩ የስዕል ስራዎችን ማበርከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም በአርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካውያን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋልም ነው ያሉት፡፡
በአርቱ ዘርፍ ያሳዩት ተምሳሌትነትና ያበረከቱት አስተዋጽኦ ሁልጊዜም የሚታወስ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለአድናቂዎቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡