Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ሳተላይት ከህዋ ያነሳችውን የመጀመሪያ ምስል ላከች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ወደ ህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ከህዋ ያነሳቸውን የመጀመሪያ ምስል ልካለች።

ምድርን እየቃኘች እና በፎቶ እየመዘገበች መረጃ የምትሰበስበውና “ETRSS-1” የሚል ስያሜ የተሰጣት የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሳተላይት የመጀመሪያ ፎቶዋን ከህዋ እንደላከች ነው የተገለፀው።

ሳተላይቷ ቻይና ከሚገኘው የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ባለፈው አርብ ነበር የመጠቀቸው።

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናት እና ምርምሮችን ለመሥራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት ተግባራትን ለማከናወን ታስችላለች ነው የተባለው።

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ይህን የመጀመሪያ ምስል ይፋ አድርገዋል፤ ሆኖም ምስሉ የት አካባቢን የሚያሳይ እንደሆነ አልተመለከተም።

Exit mobile version