አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው በወረዳው ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና አምስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡
1 ሺህ 480 አባወራዎች ደግሞ ተፈናቅለው በቢፍቱ ከተማ የተጠለሉ ሲሆን ጊዜያዊ እርዳታ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስና መረጋጋት ለማስፈን እየተሰራ መሆኑንም አስተዳዳሪው ገልፀዋል፡፡
በተስፋዬ ምሬሳ