የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

December 25, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በእንጦጦና አካባቢው የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡