አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ6 ሺህ 546 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 723 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 269 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም 500 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 43 ሺህ 119 ደርሷል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት የ13 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 365 መድረሱን ገልጸዋል፡፡