አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ፋውንዴሽን መሰረቱ፡፡
ፋውንዴሽኑ “ሃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን” በሚል ስያሜ የተመሰረተ ሲሆን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ሰርተፊኬት አግኝቷል፡፡
አቶ ሃይለማርያም የቀድሞው አሳሪ ህግ ተነስቶ ተጠቃሚ በመሆናቸው እና በአጭር ግዜ አገልግሎት በማግኘታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ፋውንዴሽኑ የእናቶችና ህጻናት ጤና እና ስነምግብን በማህበረሰብ መካከል ማዳበር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአካባቢ ጥበቃ እና ኢኮቱሪዝም ማስፋፋት እና የሴቶችና ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የማሳደግ ዓላማ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ከኢትዮጵያ አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ለመስራት ስትራቴጂክ እቅድ መነደፉንም ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው የቀድሞው አዋጅ በብዙ መልኩ ገዳቢ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
አሁን ላይ በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረጉ በየግዜው አዳዲስ ድርጅቶች እየተቋቋሙ ነው ብለዋል፡፡