Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኡበር ተባባሪ መስራች ትራቪስ ካላኒክ ከቦርድ አባልነታቸው ሊለቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012(ኤፍቢሲ) ኡበር የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ተባባሪ መስራች ትራቪስ ካላኒክ በዓመቱ መጨረሻ ከቦርድ  አባልነታቸው ሊለቁ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

ይሁን እንጂ የ43 ዓመቱ ትራቪስ በድርጅቱ ውስጥ ካሉ ዘጠኙ ዳይሬክተሮች ውስጥ አንዱ ሆነው የሚቀጥሉ መሆኑን  ነው የተናገሩት።

ትራቪስ ካላኒክ  እንደ አውሮፓውያ ኑ አቆጣጠር 2017 ላይ በድርጅቱ በተስተዋሉ የተለያዩ የሙስና ቅሌቶች  ምክንያት ስራ ለማቆም ጫፍ ደርሰው  ነበር ።

ይህን ተከትሎም  በኡበር ድርጅት ውስጥ  ያላቸውን  አብዛኛውን የአክሲዮን ድርሻ መሸጣቸው ነው የተነገረው።

ትራቪስ ካላኒክ በአስር ዓመቱ መገባደጃ  ኩባንያው ያለው የሕዝብ ግንኙነት እና በጎ አድራጎት ላይ ለማተኮር ለእኔ ትክክለኛ ጊዜ ይመስለኛል፤ በዚህም ደስተኛ ነኝ ተናግረዋል ፡፡

ካናኒክ በጣም ዝነኛ የሆነው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በመመስረት በዓለም ዙሪያ የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ  ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

ምንጭ፣ ቢቢሲ

Exit mobile version