Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሀገር ግንባታ ሂደት የማያልቅ ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ የሚሰራ ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ላለፉት ሶስት ቀናት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት እና የሰላም ፎረም ተወካዮች የተካሄደው የስልጠናና የምክክር መድረክ ተጠናቋል።
በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተገኝተው ለተማሪዎች የህይወት ልምዳቸውንና መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሚኒስትሯ በወቅቱም ሀገር በዜጎች ልቦና ውስጥ ነው የምትሰራው፣ የሀገር ግንባታ ሂደት የማያልቅ ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ የሚሰራ ነው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት ጅረት የሚፈስባቸው ቦታዎች ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ÷ ተማሪዎች ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ቆም ብለው በውይይትና በድርድር የመፍታት ባህልን ማሳደግ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።
ሰው መርጦ ባልተወለደበት ብሔርና ማንነት ሊጣላና ሊባላ አይገባም ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪሃት÷ የችግሮች መነሻ አለመተዋወቅ በመሆኑ ተማሪዎች እርስ በርሳቸው ሊተዋወቁ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶችንና ተማሪዎችን በቅርበት የሚያገኝበትን መንገድ እያመቻቸ እና በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version