Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐዋሳ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 50 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን በማምረት ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሐዋሳ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 50 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን በማምረት ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ ጀመሩ
40 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች ከሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲሁም 10 ሚሊየን ደግሞ ከአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለትምህርት ሚኒስቴር የሚቀርቡ ሲሆን የመጀመሪያው 5 ሚሊየን ጭምብልም ርክክብ ተከናውኗል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርከ በመገኘት የመጀመሪያውን ዙር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች መረከባቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version