ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሆንግ ኮንግ ተቃዋሚዎች ለገና ዋዜማ የ‹ዝምታ ሌሊት› በሚል መፈክር ተቃውሞ ለማድረግ አቅደዋል

By Tibebu Kebede

December 24, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣2012 (ኤፍቢሲ) የሆንግ ኮንግ ተቃዋሚዎች ለገና ዋዜማ የ‹ዝምታ ሌሊት› በሚል መፈክር ተቃውሞ ለማድረግ ማቀዳቸው ተገለፀ፡፡

የሆንግ ኮንግ የመንግስት ተቃዋሚዎች በዋና ዋና የገበያ አዳራሾች የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ እና በገና ዋዜማ በታዋቁ የቱሪስት ስፍራወች የ‹ዝምታ ሌሊት› በሚል መፈክር ተቃውሞቸውን ለማሰማት አቅደዋል፡፡

ሆኖም ፓሊስ ይህን የአደባባይ ተቃውሞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል፡፡

ፓሊስ  ባወጣው መግለጫ በርካቶች በባህላዊ መንገድ የገና በዓል ለማክበር የሚሰባሰቡበትን ቲሲም ሻ ትሱይ ግዛት ለተሸከርካሪዎ ዝግ እንደማያደርግ ገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት በበዓሉ ዋዜማ ቲሲም ሻ ትሱይ ግዛት ለተሸከርካሪዎች ዝግ አይሆንም ያለው ፓሊስ ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር በርካታ ፓሊሶች እንደማይሰማሩም አስታውቋል፡፡

የማህበራዊ ሚዲያ ተቃውሞ ፎረሞች  በገና ዋዜማ በተለያዩ የገበያ አዳራሾች ተቃውሟ እንደሚያደርጉ ሲገልፁ ሌሎች ተቃዋሚዎች በበኩላቸው  በቲሲም ሻ ትሱይ ግዛትና ተቃውሞ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡

በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የተሳተፉበትን ተቀውሞ ከዚህ በፊት ያካሄደው የሲቪል ሰብዓዊ መብት ግንባር በአዲስ ዓመት በሚከበርበት ቀን ሌላ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ማቀዱ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ