Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለተላመደ ቲቢ ታካሚዎች የተመጣጠነ ምግብ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለተላመደ ቲቢ ታካሚዎች የተመጣጠነ ምግብ እየተሰራጨ መሆኑን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ።።
ምግቡ እየተሰራጨ የሚገኘው መድሃኒት በተላመደ የቲቢ በሽታ አማካኝነት ሰውነታቸው በምግብ እጦት ለተጎዱ ሕሙማን መሆኑን በኤጀንሲው የቲቢ እና የወባ ግብዓት አቅርቦት ተጠሪ ባለሙያ ወይዘሪት ሜሮን ያዕቆብ ገልፀዋል፡፡
ሠውነታቸው በቂ የተመጣጠነ ምግብ ካለማግኘቱ የተነሣ ከባድ ጉዳት ለደረሠባቸው ታካሚዎች ምንም የምግብ ዝግጅት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ የሚወስዱት የተመጣጠነ ምግብ እየተሰራጨ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የሚሰራጨው ምግብ ቀለል ያለ የሠውነት ጉዳት ለደረሠባቸው ታካሚዎች የሚያገለግል ምግብ መሆኑን አስረድተው ማሟያ ምግቦቹ 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
በሲሳይ ጌትነት
Exit mobile version