የሀገር ውስጥ ዜና

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

By Meseret Demissu

October 08, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በደቡብ ወሎ ዞን አልቡኮ ወረዳ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ21 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመረቀ።

በዞኑ አልቡኮ ወረዳ ጦሳ ፊላና ቀበሌ የተገነባው አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው የተጀመረው በ2011 ዓ.ም እንደሆነም ታውቋል።