ስፓርት

ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በለንደን ላስመሰገቡት ውጤት ምስጋና አቀረቡ

By Tibebu Kebede

October 04, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በለንደን በተካሄደው የወንዶች ማራቶን አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አስደናቂት ውጤት አስመዝግበዋል ሲሉ አስፍረዋል።

አትሌት ሹራ ቅጣታ የ2020 የለንደን ማራቶንን በማሸነፉ እንኳን ደስ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሄዳችሁበት ሁሉ የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋችሁ የምታውለበልቡ ጀግኖች ሯጮቻችን ሁሉ አድናቆቴ ይድረሳችሁ ፤ ሀገራችን ትኮራባችኋለች ብለዋል ባስተላለፉት መልዕክት።

ሲጠበቅ የነበረውን የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊው ሹራ ቅጣታ ቶላ  ሲያሸንፍ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሲሳይ ለማ ሶስተኛ ደረጃን ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው።

ሹራ ቅጣታ ቶላ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ውድድሩን ያሸነፈው።

ኢትዮጵያውያን ሞስነት ገረመው ፣ ሙሌ ዋሲሁን እና ታምራት ቶላ ከ4 እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።