Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የለንደን ማራቶንን ኢትዮጵያዊው ሹራ ቅጣታ ቶላ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሲጠበቅ የነበረውን የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊው ሹራ ቅጣታ ቶላ ሲያሸንፍ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሲሳይ ለማ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
ሹራ ቅጣታ ቶላ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ውድድሩን ያሸነፈው።
ውድድሩን ሊያሸንፍ እንደሚችል በከፍተኛ ሁኔታ ሲጠበቅ የነበረው ኢሊውድ ኬፕቾጌ 8 ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
ኬንያዊው ቪንሴንት ኪፕቹምባ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ሞስነት ገረመው ፣ ሙሌ ዋሲሁን እና ታምራት ቶላ ከ4 እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
Exit mobile version