Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውጪ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውጪ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ቀነኒሳ በቀለ ከውድድሩ ውጪ የሆነው በግራ ባቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት እንደሆነ ተናግሯል፡፡

አትሌቱ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ውድድሩን ባለመሳተፌ በጣም አዝናለሁ ብሏል፡፡

ለውድድሩ ዝግጅት እንዳደረገ የገለፀው አትሌቱ በመጨረሻዎቹ የዝግጅት ሳምንታት ውስጥ በግራ ባቱ ላይ ያጋጠመው ጉዳት እንቅፋት እንደሆነበት ተናግሯል፡፡

Exit mobile version